የቡታጅራ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በክልልና በፌዴራል ደረጃ ውድድር ባገኘው አመርቂ ውጤት አስመልክቶ የእውቅናና ሽልማት ስነ-ስርዓት አካሂደ
የምስራቅ ጉራጌ ዞን ዋና አስተዳደሪ አቶ ሙስጠፋ ሀሰን በመክፈቻ ንግግራቸው ኮሌጁ ከለውጡ በኋላ ተስፋ ሰጪ ውጤት እያስመዘገበ መሆኑን ገልፀዋል።
በአገር አቀፍ ደረጃ ሞዴል የሚሆን ስራ እየሰራ ያለ ተቋም መሆኑን፤ ትውልድ የሚቀይር ፤የአርሶ አደሩን ችግር የሚፈታ ስራ እየሰራ ያለ ተቋም መሆኑንም ገልፀዋል።
ኮሌጆች ለስራ ዕድል ፈጠራ ትልቅ ድርሻ አላቸው መደገፍ ያስፈልጋል። እንደሀገር የተጣሉ ግቦችን ለውጤት ላበቁ ሁሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የዞኑ የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና መምሪያ ኃላፊ አቶ አህመዲን ጀማል የቁርጠኝነት የትጋትና የፈጠራ ስራ ስኬታማነት ማረጋገጥ ያስቻለ ውጤት ስለመሆኑ ገልፀዋል።
እምቅ አቅም እና ቁርጠኝነት የሚያሳይ ውጤት መሆኑን አንሰተው በቀጣይም በሌሎችም ዘርፎች አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ተናግረዋል።
የኮሌጁ ዋና ዲን አቶ አብድልዋሂድ መሃመድ ኮሌጅ በአገር አቀፍ ደረጃ ተወዳድሮ አመርቂ ውጤት በማስመዝገቡ በክልል እና በፌዴራል ደረጃ እውቅናና ሽልማት ተበርክቶለታል።
በአገር አቀፍ ደረጃ 2ተኛ በመውጣት የብር ሜዳሊያ ሰርተፍካትና የ4 መቶ ሺ ብር ሽልማት ተበርክቶለታል በተመሳሳይ በክልል ደረጃ 2የወርቅ ሜዳሊያ 98 ሺህ ብር እና ተበርክቶለታል ለውጤት ላበቁ ሁሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የቡታጅራ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በክላስተር ፣በክልል እና በፌዴራል ደረጃ በተግባራዊ ጥናትና ምርምር ፣በክህሎት እንዲሁም በቴክኖሎጂ ውድድር ተወዳድሮ ባገኘው አመርቂ ውጤት ምክንያት በማድረግ የእውቅናና የሽልማት ፕሮግራም እያካሂደ ነው።
በስነ-ስርዓቱ የክልሉ የሙያ ፍቃድ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ራህመቶ ቦካ ፣የዞኑ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ የተከበሩ አቶ እንዳልካቸው ጌታቸው ሌሎች የክልሉ፣የዞን የከተማና የወረዳ አስተዳደር የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
ግንቦት 13/2017 (የቡታጅራ ከተማ የመንግስት ኮሙኒኬሽን)
ተጨማሪ መረጃ የምናደርሳችሁ ይሆናል









Leave a Reply